top of page

የአማራ ክልል ታጣቂና የፀጥታ ሃይሎች በወሎ ኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ ሌላ ጥቃት እያደረሱ ነው::

(የኦነግ-ኦነሠ ጋዜጣዊ መግለጫ)

ከትናንት ጁላይ 10/2022 (እኤአ) ጀምሮ የአማራ ፋኖ ታጣቂዎች እና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በጅሌ ዱሙጋ ወረዳ በበቴ መንደር በወሎ ኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ ነው። ጀግኖቹ የወሎ ኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል ከባድ ተጋድሎ እያደረጉ ቢሆንም የክልሉ ልዩ ፖሊስ እና የፋኖ ሚሊሻ ታጣቂዎች ከፍተኛ የመሳሪያና የሰው ሀይል የበላይነት እንዳላቸው ታውቋል። እስካሁን በተደረገው ጥቃት 9 ሰላማዊ ዜጎችን ገድለው 25 ያቆሰሉ ሲሆን ወራሪዎቹ የክልሉ የጸጥታ ሃይሎች የቆሰሉ ንፁሀን ዜጎች ህክምና እንዳያገኙ እየከለከሉ እንደሆነ አረጋግጠናል። በኤርፋታና ግድም አጣዬ ከተማ አካባቢ ከባድ ውጊያ ስለመደረጉ እስካሁን የደረሰን መረጃ ባይኖርም የአማራ ልዩ ሃይል በአጣዬ ከተማ አካባቢ ሌላ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጀ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የፋኖ-አማራ ልዩ ሃይል ጥምር ሀይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከከፈቱት ወረራ ባሻገር ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር እስካሁን ድረስ ያደረጉት ውጊያ የለም። ይሄን አስመልክቶ የሚነዙት ወሬዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን እንገልፃለን።

የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛው ዕዝ ጁላይ 11፣ 2022

2 views0 comments
bottom of page